Skip to content

የአዳም ቀለማት

July 4, 2013

አዳም ረታ የዘመኑ ስጦታ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ ይፅፋል ይፅፋል ይፅፋል፡፡ አጫጭር ልብወለዶችን ግሩም ይሰራቸዋል፤ ገፀ ባህሪያትን እንደ አዳም የሚስል፣ የሚገልፅ ደራሲ ማግኝት ሳይቸግር አይቀርም፡፡ የአዳም ብቸኛው ረዥም ልብ ወለድ የሆነው ‹ግርጫ ቃጭሎች› የዘመናዊ አማርኛ ስነ ጽሁፍ ጥግ እንደሆን ሀያሲያን እና ጠበብት ይናገራሉ፡፡ የግርጫ ቃጭሎቹ ዋና ገፀ ባህሪ ‹መዝገቡ› አስገራሚ ፍጡርነት እና እሳቤ፤ አዳም ግን መዝገቡን እንዴት አሰበው? እንዴትስ ሰራው; ያስብለናል፡፡ ወይ የእሱ (የአዳም) ስራ እንድንልም ያስገድደናል፡፡ አሁን ደግሞ አዳም ‹የስንብት ቀለማት› ባለው ረዥም ልብ ወለዱ ብቅ ሊል ነው፡፡ አይን መክፈቻ (Appetizer) ይሆንም ዘንድ ከመፅሃፉ የመጀመሪያ ገፆች እነሆ ብሎናል፡፡

በዚህ በአዲስ ስራው፤ ተኮላ እና ጅማወርቅ የተባሉ ባልና ሚስቶች ስለትዳራቸው፤ ስለ ኑሮ፤ ስለ ውበት፤ ስለ ወሲብ ለአንባቢው እየተናገሩ፤ አለፍ ሲልም እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ አብረውን ይከተሉናል፡፡ አዳም ውብ ቃላት በአፍ በአፋቸው እያጎረሳቸው እነሱ ይተፋሉ፡፡  እኔም በአዳም ገለፃዎች ተደምሜ ከጅማ ወርቅና ከተኮላ ንግግሮች እንዲሁም ተግባራት በትንሹ አቅርቤያለሁ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የመፅሃፉ ዋና ገፀ ባህሪ ተኮላ ሚስቱን ጅማወርቅን ከሌላ ሰው ጋር ስትላፋ እና ስትሳሳቅ አይቷት ደነገጠ ደንግጦም አልቀረ ይለናል አዳም፡

‹‹ተኮላ ፈሱ አመለጠው፡፡ ደነገጠም፡፡ ከሁሉ ያስደነገጠው የፈሱ ድምጽ ከሰው አንደበት የወጣች መምሰሏ ነው፡፡ የሆነች እንስትነት አላት፡፡ ድሮ የሚያውቃት በትንሹ የረሳት ሴት ድምጽ፡፡›› እያለ ተኮላ የመፍሳት ሱስ እንደተጠናወተው ደጋግሞ ይነግረናል፡፡ የተፈሱ ፈሶችን በሙዚቃ ኖታ ይደረድራቸዋል አዳም፡፡ እንደዚህ:

ፈስ – 1

1

2. የፈስ ስኪዞፌሪኒያ

2

ፈስ – 3

3

4. የፈስ ኢል ኒኞ

4

ፈስ – 5. ‹‹ሊቆጥራቸው ያልቻለ እንደ ሰንሰለት የተያያዙ ከመሃላቸው ደካማ ሰከንዳዊ ረፍት ያስገቡ ጡጦችና ቁቆች ፓራሞችና ዘረጦች እያከታተለ ለቀቀ››

5

6. “የወረወረው ማስታወሻ መቀመጫውን እንደነካ ቆጣ ያለች አጭር ፈስ አመለጠችው”

6

በመጨረሻም፡

 

እስኪ አዳም ሙሉውን መፅሃፍ ያሳትምልን እና ደስታን እንመገብ፡፡

From → Random resources

Leave a Comment

Leave a comment