Skip to content

መፅኃፍት ስለ አፄ ቴዎድሮስ

February 8, 2012

ታሪክ ሲባል እንግዲህ ውዝግቡ ብዙ ነው ፡፡ ታሪክ አይጠቅምም ከሚለው እስከ ታሪክ እንጀራቸው የሆነ ያክል ሙጭጭ ብለው እሰከያዙት ሁለት ጫፎች ድረስ፡፡ በመሃል ብዙ ውዝግቦች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው፡፡ እንደኛ ባለ ታሪኩ (የተፃፈውም ያልተፃፋውም) ተወሳስቦ ባለበት ሀገር ደግሞ ጣጣው እና ትርጉሙ ብዙ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ  ሲባል ገና የየትኛዋ ኢትዮጵያ ታሪክ ; የ 100 ዓመቷ  ናት የ 3000 ዓመቷ ; ብለው ከሚጠይቁ አስከ የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ የጭቆና እና የመከራ ነበር አልፎም ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች (የጎሳዎች) እስር ቤት እና የነጭ ጋቢ ለባሽ እና የዶሮ ወጥ ተመጋቢ  ቅኝ ገዥ እና የቡና ለቃሚ  እና የአደን አዳኝ ቅኝ ተገዥ ግንኙነት ነበር ከሚሉ የሲኦል ምስል ሰባኪዎች እስከ አይ ኢዮጵያማ ሀገረ-ሰላም፣ የኩሩ ህዝብና እና የድንቅ ባህል ሀገር እንዲሁም ለጠላቶቿ እሳት ለወዳጆቿ ገነት የነበረች ምድረ ገነት ነበረች እስከሚሉ የገነት ምስል ሰባኪዎች ድረስ፡፡

እኔ በበኩሌ ታሪክ ደስ ይለኛል ቢያንስ ለሀሴት(Pleasure ) እና ለእውቀት(Knowledge ) ሲባል በሚለው ሀሳብ ተመስርቸ፡፡ ማንም ሀገር ነጭ ወይም ጥቁር ታሪክ ነበረው/ አለው አልልም፡፡ ሁሉም ባለ ግራጫ  ታሪክ ነው ባይ ነኝ፡፡

ከኢዮጵያ ታሪክ ጋር አብረው ከሚነሱ ጥቂት ስብእናዎች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ ከላይ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚነሳው ውዝግብ በአፄ ቴዎድሮስም ላይ መነሳቱ አልቀረም፡፡ እንደዚህ አይነት፡

<<አፄ ቴዎድሮስን ያገነናቸው ደርግ ነው፡፡ ደርግ ጃንሆይን ለማንኳሰስ ሲል የድሃ ልጅ ጀግና ሲፈልግ ቴዎድሮስን እና በላይ ዘለቀን አገኝ የጀግንነት ቅባም ቀባቸው እንጅ ቴዎድሮስማ ያው የኮሶ ሻጭ ልጅ ናቸው፡፡>>

<<አፄ ቴዎድሮስ ያለጊዜያቸው የተወለዱ፣ዘመናቸውን የቀደሙ፣ ንጉስ ሀሙራቢ የተበታተነችውን ባቢሎን አንድ አድርጎ ታላቅ ግዛተ-አፄ እንደመሰረተው አፄ ቴዎድሮስም የተበተነች እና ደካማ ኢትዮጵያን አንድ አድርገው  በዘመናዊነት ፈረስ ላይ ኢትዮጵያን የጫኑ እፀብ ድንቅ መሪ ናቸው፡፡>>

<<ቴዎድሮስ ተስፋፊ እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈፅሙና ሰያስፈፅሙ የነበሩ ከመሆናቸውም በተጫማሪ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ችግሮች ጀማሪ እና ጠንሳሽ ነበሩ፡፡>>

<<ቴዎድሮስ የሃገርን ፍቅር ልክ እስከምን እንደሆነና ለሃገር የሚገባት ክፍያ ምን ድረስ እንደሚዘልቅ ያስተማሩ እና ምሳሌ የሆኑ ታላቅ ንጉስ እንዲሁም ሀይማኖትን ከመንግስት ለመለየት (የቤተክርስትያንን ጳጳስ እስከማሰር የደረሱ) ታላቅ ጥረት ያደረጉ አቢዮተኛ መሪ  ናቸው፡፡>> ወዘተ፡፡

የሆነው ሆነና አስኪ ስለ አፄ ቴዎድሮስ የተፃፉ ፅሁፎችን ሰፊው ህዝብ አንብቦ ይፍረድ በማለት ከዚህ በታች አምስት መፅኃፍትን አስቀምጠና፡፡ ያንብቡ፣ ይደሰቱም፡፡

 

የቴዎድሮስ ታሪክ

በደብተራ ዘነበ

ያጤ ቴዎድሮስ ታሪክ

ባልታወቀ ሰው

የዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ታሪክ

በአለቃ ወልደ ማርያም

አጤ ቴዎድሮስ

በጳውሎስ ኞኞ

አፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት

በተክለ ፃዲቅ መኩሪያ

 

From → Random resources

8 Comments
 1. alemayehu permalink

  በጣም ከወደድኳቸው እና ካከበርኳቸው ሳይቶች አንዱ መሆኔን ስገልጽ በደስታ ነው፡፡ በጣም ጠቃሚና ውብ መጻህፍቶችን እያቀረብክልን ስለሆነ በእውነት ምስጋና ያንስሃል፡፡ በአጭሩ እግዚአብሄር ይስጥልኝ ማለቱ ልብ የሚሞላ መስሎኛል- እባክህ ትርታ አዳማጭ ነህና በዚሁ ቀጥል፡፡

  ሞቅ ካለ ሰላምታ ጋር

  አለማየሁ ገበየሁ

 2. Really Amazing & Interesting historical events thanks for shearing !

 3. Elenni permalink

  ወንድማችን ለማንበብ ያለህን ፍቅር በጣም አደንቃለሁ፣ ከዚህም የተነሳ ሌሎችም እንድናነብ የምታደርገውን ጥረት ደግሞ በእጅጉ አደንቃለሁ፣ በርታ የሚያሰኝ ስራ ነው ያለንን፣ ያወቅነውንና ሌሎች ቢያውቁት በለን የምናስበውን ማካፈል ጥሩ ልምድ ነው፡፡
  በተለይ ደግሞ እዚህ ኢትዮጵያ ያለን ሰዎች ልናገኛቸው የማንችላቸውን መጽሐፍቶች ባንተ ድረ ግጽ ላይ በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል በዚሁ ቀጥል እግዚአብሔር ይስጥልን ብለናል፡፡
  ከድረ ገጽህ ተከታታዮች አንዷ!

 4. alemu permalink

  ዘላም ከአንተ ብዙ መማር እንችላልን ስንል ከጎናችን እራቅህ ነገርግን በሌላ አቅጣጫ አገኘንህ በርታልን ዘላለም

 5. Etiopiawi permalink

  እግዚአብሔር ይስጥህ። ምስጋናዬና አድናቆቴ ከልብ ነው።

 6. Mulu permalink

  እነዚህ መፃህፍትን በተለይም የ “ጳውሎስ ኞኞ”ን ማግኘት ቸግሮኝ ነበር፡፡ “ባልታወቀ ሰው የሚለውን ግን down load ማድረግ አልጃልኩም፡፡ ለሁሉም እጅግ አመሰግናለሁ!

 7. That is wonderful work. God bless you!!!!!!!!!!!!!!!!!! keep it up!!!!!!!!!!!!!!

 8. Hasen permalink

  የአፄ ቴዎድሮስ ሃቆች፡-
  (ከቲፎዞነት ሃቀኝነት ይቅደም!)
  ስለ አፄ ቴዎድሮስ ማንነትና ባህሪ በአገር ውስጥና በውጭ ምሁራን በትክክል ተፅፈው የሚገኙ ብዙ ሃቆች ቢኖሩም ብዙውን ጊዜ ግን ልቦለድ ድርሰቶችና የአዝማሪ ቤት ሙገሳዎች ሲጮህ ይሰተዋላል፡፡
  ጥቂት ስለ ሃቁ፡-
  1- ጭካኔ
  -በኢትዮጵያ ታሪክ ቤተክርስቲያን ያቃጠሉ ብቸኛው ንጉስ
  -ወደ መቅደላ ሸሽተው በተሰደዱበት ወቅት ደብረ ታቦር ከተማን ሙሉ በሙሉ በእሳት ያቃጠሉ
  -ጎንደር ቤተመንግስትና ቤተክርስቲያንን ያቃጠሉ
  -ሴቶችና ህፃናትን ሳር ቤት ውስጥ አጉረው ያቃጠሉ
  -የሰው ልጅ ከነነፍሱ እጅ እግሩን ብቻ ቆራርጠው ገደል የወረወሩ
  -በመድፍ ጥይት ሰው የረሸኑ በታሪክ ብቸኛው ሰው
  -ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረጉት አንድም የቃል ንግግር የሌላቸው፤
  -በአንፃሩ ስልጣናቸውን ካጡ ተመልሰው ዘረፋ እንደሚገቡ ደጋግመው ይዝቱ የነበሩ
  -አገር በሙሉ ይጠላቸው የነበረና ራሳቸውን ባጠፉ ጊዜ ሬሳቸውና የሚያነሳው ጠፍቶ ቀኑን ሙሉ ፀሃይ ላይ የዋለ፡ልጆቻቸውን ለመረከብ አንድም ዘመድ እንኳን ያልተገኘ
  -በቤተ ክርስቲያንና በአገር ደረጃ በጥቁር ታሪክ የሚታወቁ
  (እዚህ ላይ ግን የቴዎድሮስን ስራ ደርግ ለክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ማጀቢያነት እና የሰውን ልጅ የጭካኔ ጥግ ያሳየበት ለአረጎራው ቀረርቶነት የተጠቀመበት ዘመን ብቻ ሳይጠቀስ አይታለፍም)
  2-ባህሪ
  -ዘወትር ይሰክሩ የነበሩ
  -ማታማታ ልብሳቸውን እየቀየሩ ባል የሌላቸው ሴቶች ቤት ይሄዱ የነበሩ
  -አገርና የውጭ ሰዎች እብዱ ንጉስ እያለ ይጠራቸው የበሩ
  3-መልካቸው(የማይነገረው)
  -መልካቸው ከመደበኛው ኢትዮጵያዊ በተለየ መልኩ በጣም ጥቁር የነበሩ(ዘራቸው ግን ሻንቅላ ወይም ሱዳናዊ ያልሆኑ)
  -አይናቸው አነስ አነስ ያሉና ገባ ገባ ያሉ

  እነዚህ ጥቂቶቹ ሲሆኑ የመረጃ ምንጭ፡-
  የራሳቸው ታሪክ ፀሃፊ አለቃ ዘነብ፡የታሪክ አባት ተክለፃዲቅ መኩሪያ፡ጳውሎስ ኞኞ፡ሉዊስ ክራፍ፡ሄነሪ ስተርን…
  አመሰግናለሁ፡፡
  ታሪክ ተፈጥሯዊ እንጂ ፈጠራ አይደለችም!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: