Skip to content

መግለጫ በኢትዮጵያ፡ ትናንት እና ዛሬ

January 22, 2012

የጋዜጣዊ መግለጫ እና የአቋም መግለጫ ነገር ሁሌ እንዳስገረመኝ ነው፡፡ እንዴት  ብሎ መጠየቅ  መልካም ነው አበው እንደሚሉት “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ነውና ነገሩ፡፡ ደስታ ተክለወልድ  “ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት” በተሰኝው መፅሃፋቸው  መግለጫ የሚለውን ቃል “ማስታወቂያ  መንገሪያ  ነገር ወይም  የመጽሐፍ  መግለጫ ለጠንቋይ የሚሰጥ ገንዘብ ነው” ብለው ይፈቱታል፡፡ ይህ ትርጉም በዕውነት መግለጫ አሁን ካለው ትርጉም በ እጅጉ ይርቃል ዛሬ መግለጫ ሌላ ናት እንደ ሃሳብን ማስታወቂያ እንደ ሆኔታን መገምገሚያ፡፡ “መግለጫዎችን” ስሰማ ግራሞቴን የሚጭሩት የቃላቶቹ አመራረጥ፣ የሃሳቦቹ አስቂኝነት፣ የባለ መግለጫዎቹ ማንነት ወዘተ ናቸው፡፡

ለምሳሌ ደርግ እንዲህ ብሎ መግለጫ ይሰጥ ነበር”

<<በጩኸት የፈረሰች ከተማ እያሪኮ ብቻ ነች !!!>>

<<ነጭ ኑግ ጥቁር ወተት አቅርቡልኝ ለሚል ህዝብ አቢዮታዊ እርምጃ እንጅ በ Demand-Supply ጨዋታ ጊዜያችንን አናጠፋም !!!>>

<<የመርጦ ለማሪያም ከተማ ህዝብ የሬጋንን አስተዳደር አወገዘ የአለም ሰራተኞችም እንዲተባበሩ ጋበዘ!!! >> …

እነ ጋሽ መለስ ወደ ስልጣን መጡና ደግሞ ህዝቡን “ልማት ወይም ሞት” ምናምን ብለው አስጨፈሩት መግለጫቸውንም እንዲህ አስከተሉ:

ዘንድሮ በተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ላይ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ

♥ እኛ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች  ምንም እንኳን  ♥ፍቅራችን♥ የ 20 ዓመት (ከ1983 ዓ.ም) ለጋ ፍቅር ቢሆንም፣ ♥በፍቅራችን♥ መሃል የሚገቡትን ማንኛውንም የኒዮ-ሊብራል ሃይሎች እናወግዛለን መንግስታችንም በአሸባሪነት እንዲፈርጅልን እንማፀናለን፣

♥ “ጥፋተኛ፣ ጥፋተኛ ወታደር ነው ነገር ግን ባላገር ይካስ” በሚል መርህ የአለማቀፉ ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ አንቀበልም ብቻ ሳይሆን እንቀደዋለን፣

☂ የአባይን ግድብ እንገድበዋለን ኢህአዴግንም ደጋግመን እንመርጣለን ፣ኪራይ ሰብሳቢ ሁላ ምን ትሆኝ እንግዲህ

Human Rights Watch, CPJ & Amnesty International ከአስመራ መንግስት ጋር ያላቸውን ግንኝነት ደርሰንበታል ይሄም ዘማዊ ግንኙነት” ውሻ ምን አገባት ከ እርሻ” የሚለውን የአማራ ተረት ፣ “አብያ በረ በረ እንቃርነረ” የሚለውን የጉራግኛ ተረት፣ “ወረያ ዙሚል ባሚል ቱም” የሚለውን የሶማሊኛ ተረት እና ወዘተ ተረቶችን ያስታወሰን ሲሆን ለትውስታው እያመሰገንን ለተግባሩ ግን ዋ! ዋ! ዋ! የሚለውን የጀኔራል መንግስቱ ንዋይን ማስጠንቀቂያ ጋብዘናችዋል

☂ሀገራችን ኢትዮጵያን ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት አድርጎ ፣ ለንጉሳችን እድሜ ርዝመት፣ ለግዛቱ ስፋት፣ ለመንግስቱ ፅናት ይስጥልን፡፡

የማይታይ የከ80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ፊርማ አለበት

ህገ-መንግስቱን ለሚንዱት አይደለም ለሚገላምጡትም ወደኋላ አንልም

ይህ እንግዲህ በብሶት በወለደው በጀግናው የሰሜኑ ኮከብ ኢህአዴግ ጊዜ እና አኳያ ነው፡፡

ደግሞ አለላችው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ሙያ ማህበራት መግለጫ፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ

♣ <<የአቢዮቱ ቀለም ኢትዮጵያዊ ነው>> (ኢህአፓ በGeorgia & Ukraine Color Revolution ሰሞን የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ )

♣ <<ከመለስ ዜናዊ የማይሻል የለም>> (ግንቦት 7)

♣ <<የህዝብ ገንዘብ የማርያም ፀበል አይደለም>> ( የኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር)

♣ <<መፃፍ አሸባሪነት ከሆነ፣ አዎ ገና ብዙ እናሸብራለን>> (ውጭ ያለው ኢነጋማ)


ነገስ እንዴት ይሆን?

From → Articles

3 Comments
  1. Misganu permalink

    Y aha!! I wonder a person those … 10Q

  2. ayenachew permalink

    good observation! I think we r not lucky…we need to try more patiently to come up with better..

  3. Mezgebu permalink

    You know what Zola…I am very happy to know someone like you.. Thanks !! …BTW…thanks again for the books..

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: