Skip to content

ነገረ ሼኽ ሁሴን ጅብሪል

March 30, 2011

በትንቢት አላምንም:: ነገር ግን ‘የሼኽ ሑሴን ጅብሪል ትንቢቶች’ እየተባሉ የሚነገሩት ግጥሞች ውበታቸው ደስ ስለሚለኝ ብቻ “እውነት በሆኑ” ማለቴ አልቀረም:: እንደማይሆኑ ውስጤ ቢነግረኝም:: “እኔው ብቻ አንብቤያቸው ከምስቅ ሌሎችም ያንብቧቸው” በሚል ለማጋራት ነው ይሄን መለጠፌ::

‘የሕይወት ታሪካቸውን’ከአፈ ታሪኩ በመቀላቀል ዶር ጌቴ ገላዬ ‘ሼህ ሁሴን ጅብሪል እና ትንቢታዊ ግጥሞቻቸው’ በሚል ርዕስ ካዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ በረጅሙ ጠቅሼ ወደ ግጥሞቹ አልፋለሁ::

ሼህ ሁሴን ጅብሪል ከ1811- 1908 እንደኖሩ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ቤተ በመጽሐፋቸው ጠቅሰዋል። ስለ ሸህ ሁሴን ጅብሪል የሕይወት ታሪክ በስፋት የጻፈ ቦጋለ ተፈሪ በዙ ነው:: አቶ ቦጋለ ተፈሪ ፣ ሼህ ሁሴን ጅብሪል ከአባታቸው ከሼህ ጅብሪል በወሎ ክፍለ ሀገር በወረሄመኖ አውራጃ፣ በባዙራ ምክትል በባሆች ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ እምበለ ሴዳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በ1811 ገደማ ተወልደው በ97 ዓመታቸው አንዳረፉ ጽፈዋል:: አባታቸው በዘመኑ በቃሉ አውራጃ ታዋቂ ለነበሩት ለገታው ሼህ ቡሽራ አድረው ለሰላሣ

ዓመታት በመውሪድነት አገልግለዋል:: ጌታው ሼህ ሁሴን መፍረ የጀመሩት ገና በሰባት ዓመታቸው እንደሆነና የሚናገሩትም መሬት ጠብ እንደማይል ተጽፏል:: አሐዱ ወይም ቢስሚላሂ ብለው ፍርድ የጀመሩት በአጼ ዮሐንስና በመምሬ ግርማ በተባሉ ቄስ ነው ይባላል። እየታወቁ ሲመጡ ወደፊት የሚሆነውንና የሚመጣውን ከነመፍትሔው መናገራቸውና መተንበያቸው ነበር:: የሚናገሩትም በግጥም ነበር። ከዚያ ነገሥታቱም፣ መሳፍንቱም፣ ትንሹም ትልቁም እሳቸውን መጀን ማሌት ያዘ። ግጥሞቻቸውን ከእረኛ እስከ ቃዲ ያውቀዋል፣ይለዋል:: ሼህ ሁሴን የነቢዩ መሐመድ ተከታይ ነበሩ:: ቢሆኑም እንደ እስላሞች ጫት አይቅሙም፣ ሶላት አያደርሱም፣ መስገጃ ቁርበት፣ ውኃ መያዛ ጦሌ አያንጠለጥሉም:: እንደ ዓባይ ጠንቋይም መጽሐፍ አይገልጡም፣ ጠጠር አይጥሉም:: ግን ሱረት (ሐቀኑር) ያሸታሉ፣ ብርዝ ይጠጣሉ፣ ፍርድም ሲፈርዱ ማለት የሚታያቸውን ሲናገሩ ብርዝ በፎሌ (በሽክና) ይዘው ነበር ይባላል:: በሕይወት ዘመናቸው በጊዜው ታዋቂ ከነበሩት ባለዐቢ ከጥቅሳው ሼህ፣ ወልይና አሊም ጋር ተጣልተውና ተቃቅረው እንደነበር፣ ወዲያውም በጠና ታመው እንደነበር አቶ ቦጋለ ጠቅሰዋል። ከጥቅሳው ሼህ ጋር ጠባቸው ይፋ ከሆነ ጀምሮ በሽታቸው ጠናባቸው፣ እናም የሚከተለውን ግጥም አዜሙ ይባላል፣

በጎጃም፣ በትግሬ፣ በሸዋ፣ በጎደር ሳገሳ ሳገሳ
ስብርብር አረገኝ የጥቅሳ አንበሳ።

የተመረጡ ግጥሞች 

1.

አንድ ዓመት ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ
 አላህ መተማ ላይ ይስላል መቀስ
 በደም አጨማልቃ የምትቆራርስ
 እራስ የምትቆርጥ ያውም የንጉሥ
 አንደዜ ተመታች የማታላውስ::

2.

የምኒልክ ዘር አልቆ መነን ትቀራለች
 ተፈሪን አግብታ ዱቄት ትወልዳለች
 ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ጉድ ታያለች
 የባሏን መከራ ሳታይ ትሞታለች
 ሐበሻ የዚያን ቀን ትነፋፍሳለች

3.

ተፈሪን አውርደው ተፈሪ ከገዛ
 ለትንሽ ቀን እንጂ እጅግም አይገዛ
 ለዕለት ተጠንቀቀው አይምሰልህ ዋዛ
 በጉልበት ካልሆነ በፍቅርም አይገዛ
 ኋላ ግን ሟች ናቸው ነገሩ ከበዛ::

4.

በአሥመራ ወያኔ ከመጣ ችግር
 መጀመሪያ አሥመራ ትሆናለች ቀብር
 አክሱም ትጠፋለች በአንድ ቀን ጀንበር
 ግሼን ላሊበላ ትሆናለች ቀብር
 ሁሉም ይሸፍታል ሴት እናኳን ሳይቀር::

5.

አሥመራ ልትጠፋ ገመዱ ሲላላ
 በሸዋ ከተማ ይኸለቃል በላ
 በሦስት ቀን ይያዛል ጎንደር ላሊበላ
 አክሱም የዚያን ጊዜ ትሆናለች ሌላ
 ማርያም ትጠፋለች አያዋጣም ብላ::

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ‘ትንቢታዊ’ ግጥሞችን እዚህ ላይ በመጫን ሙሉውን ማንበብ ይችላሉ ፡፡

From → Uncategorized

One Comment
  1. fekidyiab permalink

    i like it

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: